Kelebuwa Lyrics
Haile Roots

የእውነት ነው ከልቧ
ሳይሆን የውሸት የእሷ እኔን መውደዷ
የእውነት ነው ከልቧ
የእሷ ደግነት መልካም ሴትነቷ
አይደለም ዛሬ
ቀን ካለፈ ከርሞ
መልካም ሴትነቷ
ለእኔ የታየኝ ቀድሞ
ስትመርጠኝ እንጂ
ያኔ እያለሁ ባዶ እጄን
ንቃ ብልጭልጩን
ስታንኳኳው ደጄን
መፈተኗ ነው
በእሳት እንደወርቁ
የለያት ከሌሎች
አምረው ከደመቁ
ከ እውነት ሚዛን ላይ
ተሰፍራ ከብዳለች
በህይወት ውጣ ውረድ
ተፈትና አልፋለች
ውለታዋ እጂግ ብዙነው
ለእኔ ያደረገችው
ተቆጥሮስ መች ያልቃል እና
ለእኔ የሆነችው
ሲጨንቀኝ ሳዝን ደስታዬ
ናት መፅናኛዬ
ተመርጣ የታደለችኝ
ለኔ ድርሻዬ
Translate Haile Roots - Kelebuwa lyrics to: